በሊቢያ እና በማልታ የባህር ዳርቻ ከ7 መቶ በላይ ስደተኞች ህይወት ማትረፍ ተቻለ

ሃምሌ 26 ቀን 2013(ኢዜአ) በሳምንቱ መጨረሻ በሊቢያ እና ማልታ የባህር ዳርቻ ከ7 መቶ በላይ ስደተኞች ህይወት በባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ማትረፍ ከመስመጥ መታደጉን ተገለጸ።

ከስደተኞች መካከለ 400 የሚሆኑት ሰዎች ከማዕከላዊ ሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ህይወታቸው መታደግ የተቻለ ሲሆን ተጨማሪ 100 ደግሞ ከማልታ የተነሱ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። አራት  ጀልባዎችን ማትረፍ መቻሉም ተገልጿል።  

አብዛኛዎቹ ስደተኞች ወደ አውሮፓና ጣልያን ተስፋ በማድረግ 300 ኪሎ ሜትር ገደማ  ከሊቢያ ባህር ዳርቻ መነሳታቸውም ተገልጿል።

በዚህ ዓመት ውስጥ ብቻ ጉዞውን ለማድረግ ሙከራ ካደረጉ መካከል ከ900 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ዘገባው አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም