ቀጥታ፡

''እኔ ሙሉ አካል ይዤ ቁሜ ኢትዮጵያ አትፈርስም''!

ሚዛን ሐምሌ 23/2013 (ኢዜአ) ''እኔ ሙሉ አካል ይዤ ቁሜ ኢትዮጵያ አትፈርስም!''
መንግሥቱ ጴጥሮስ  የሀገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር ከተነሱ የኢትዮጵያ ወጣቶች አንዱ ነው።

ወጣቱ የመንግሥት ሠራተኞች ጭምር የሀገሪቱን ህልውና ለማረጋገጥ ''እንዝመት'' ከሚሉበት ከቤንች ሸኮ ዞን በሀገር ወዳድነት መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ወስኗል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን አፍራሽ ጦርነት ለመመከት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁነቱን ገልጿል።

እንዲያውም ''ኢትዮጵያን የማዳን ዘመቻ አካል በመሆኑ ደስተኛ ነኝ'' ብሏል።

ወጣት ምስክር ገብረ ማሪያም ለሀገሯ ያላት ፍቅርና  የጁንታው  ጸያፍ ድርጊት አነሳስቷትወደ

 ጦር ግንባር  ለመሄድ መነሳቷን ለኢዜአ ገልጻለች።

''ሀገር ከሌለች መኖር አንችልም፤ በሀገር የመጣውን ለመመከት ቅድመ ሁኔታ መቀመጥ ስለሌለበት ሴትነቴ ሳይገድበኝ ጁንታውን ለመውጋት ተነስቻለሁ'' ብላለች።

ከቤንች ሸኮ ዞን  ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል በፈቃደኝነት መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል የወሰኑ ወጣቶች ትናንት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማን ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ  አቶ ፍቅሬ አማን ተቀብለው ተሸኝተዋል።

ዋና አስተዳዳሪ  በወቅቱ እንዳሉት ኢትዮጵያን እየወጋ ያለውን አሸባሪ ቡድን ደምስሰን እንደአባቶቻችን ገድል በመፈጸም የተረከብናትን ሀገር የማቆየት ግዴታ አለብን።

ወጣቶቹ ተገቢውን ስልጠና ወስደው ሀገርን የማዳን ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

"ኢትዮጵያ ልጆቿ እያሉ የማትፈርስ መሆኗን ከወጣቶቹ ወኔና መነሳሳት ማረጋገጥ ይቻላል " ያሉት ደግሞ የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ዳዊት ጢሞቴዎስ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም