አሸባሪው ሕወሃት ከጫካ ጀምሮ አማራውን እርስ በርሱና ከሌሎች ህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚያደርገው ሙከራ አይሳካም - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪው ሕወሃት ከጫካ ጀምሮ አማራውን እርስ በርሱና ከሌሎች ህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚያደርገው ሙከራ አይሳካም
ሐምሌ 23/2013(ኢዜአ) አሸባሪው ሕወሃት ከጫካ ጀምሮ አማራውን እርስ በርሱና ከሌሎች ህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚያደርገው ሙከራ እንደማይሳካም ።
የአሸባሪው ህወሃት ቡድን አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን በሰጠው ቃለ መጠይቅ በአማራ ህዝብና ልሂቃን ላይ የተለያዩ የሃሰት አሉባልታዎችን በመንዛት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ሲፈፅም የነበረውን ግፍና በደል እንደ ገድል ሊሰብክ ሞክሯል።
አሸባሪው ሕወሃት ከጫካ ጀምሮ አማራውን እርስ በርሱና ከሌሎች ህዝብ ጋር ለማጋጨት የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም ይህንኑ በተለያየ መልኩ እየገለፀ ይገኛል።
ይህን የአሸባሪ ቡድን የጥፋት ድርጊትና የመከፋፈል ሙከራ አስቀድሞ የተረዳው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጁንታውን ለመዋጋት እያሳየ ካለው ቁርጠኝነት ባሻገር በተግባርም ቡድኑ እየፈፀመ ያለውን ጥፋት ለማስቆም በተግባር እየተንቀሳቀሰ ነው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ፣ ለኢዜአ እንዳሉት አሸባሪው ህወሃት ከጫካ ጀምሮ አማራውን እርስ በርሱ እንዲጋጭ ሲሰራ መቆየቱንና ከዚያም አልፎ ከመላው ሕዝብ ጋር ለማጋጨት ጥረት አድርጓል፤ የሰሜን ሸዋ ህዝብ የአሸባሪውን ህወሓት ግብዓተ መሬት ለመፈፀም የአገር መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀልም ጀምሯል።
ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር በመሆንም ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ለማድረግ እየዘመተ ነው።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን የአማራ ህዝብ ከሌሎች ህዘቦች ጋር ስላለው ግንኙነት የሀሰት ትርክት በመፍጠርና በማሰራጨት ግጭት እንዲፈጠር በተደጋጋሚ ጥረት እያደረገ መሆኑን ነው አቶ ታደሰ የጠቆሙት።
ህወሃት የአማራ ህዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭ ጫካ ውስጥ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሲሰራበት መቆየቱንና አሁንም የሀሰት ሰነድ በማዘጋጀትና የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎች በመንዛት ህዝቦችን ለመከፋፈል እየሞከረ መሆኑንም አብራርተዋል።
ይህንንም ህዝቡ ጠንቅቆ የሚያውቀው ሃቅ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የአማራ ልሂቃን በተደጋጋሚ የልማት ጥያቄዎች በማንሳታቸው፣ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በመቆርቆራቸው አሸባሪው ሃይል የተለያዩ ስሞችን በመስጠት ከህዝብ ለመነጠል ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱንም አስታዋሰዋል።
አካባቢው ላለፉት በርካታ ዓመታት በአሸባሪው ህወሃት የጭቆና ቀንበር ሥር ነበር።
በህዝብ ትግል ከሥልጣን ከወገደ በኋላ ግን የዞኑ ሕዝብ የልማት ጥያቄዎቹ እየተመለሱለት ነው።
አሸባሪው ሕወሃት ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ የሰሜን ሸዋ ህዝብ ለ27 ዓመታት የቆየው የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄ እየተመለሰ መሆኑንም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ አመልክተዋል።
አሸባሪው ህወሃት ከሥልጣን ከተወገደበት አንዱ ምክንያት በተወሰኑ ሃይሎች ያልተገባ የልማት ተጠቃሚነት እየተንሰራፋ መምጣቱ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሰሜን ሸዋ ህዝብ የልማት ጥያቄ በአሁኑ ወቅት እየተመለሰ መሆኑን ጠቁመው፤ ከደብረ ብረሃን ጂሩ፣ ከለሚ ሙከ ጡሪ፣ መራ ቤቴ፣ ጃማ ደጎሎ መንገድ ከለውጡ በኋላ የተገኙና በ2010 መጀመራቸው በማሳያነት ጠቅሰዋል።
የሰሜን ሸዋና የአካባቢው ህዝብ አሸባሪው ህወሃት በአገር ላይ የፈፀመውን ክህደት ለመመከትና የቡድኑን የመጨረሻ ግብዓተ መሬት ለማረጋገጥ ቆርጦ መነሳቱንም ተናግረዋል።
እስካሁን ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ህዝቦች ሃገራቸውን ከአሸባሪው የህወሃት ቡድን ትንኮሳና ጥቃት ለመጠበቅ እንዲሁም ቡድኑን ለማስወገድ ወደ መከላከያ ሰራዊት መቀላቀላቸውን ገልጸው፤ የመንግስት ሰራተኛው፣ ነጋዴው፣ አርሶ አደሩና በሌላ ሙያ ላይ የተሰማሩ የማህበረሰብ አባላትም ሁሉ አቀፍ ድጋፋቸው እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል።