ቀጥታ፡

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ሀምሌ 23/2013(ኢዜአ) በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ተጠባቂው የ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር ዛሬ ይካሄዳል።

በዚህ የ10 ሺህ ሜትር ውድድር የማሸነፍ ቅድሚያ ግምት ካገኙት መካከል ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር በአትሌቶቿ ሰለሞን ባረጋ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ እና በርሁ አረጋዊ ትወከላለች።

በተጨማሪም ዛሬ የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ የሚካሄድ ሲሆን እጅጋየሁ ታዬ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና ጉዳፍ ፀጋዬ የማጣሪያ ውድድራቸውን ያካሂዳሉ።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ትናንት ምሽት የ800 ሜትር ሴቶች እና የ3 ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናከል የማጣሪያ ውድድር አካሂደዋል።

በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ሀብታም ዓለሙ ማጣሪያውን ስታልፍ አትሌት ነጻነት ደስታ ማጣሪያውን ማለፍ ሳትችል ቀርታለች።

በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ጌትነት ዋለና ለሜቻ ግርማ ማጣሪያውን ሲያልፉ ታደሰ ታከለ በማጣሪያው ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም