ቀጥታ፡

አሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ለዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ቆመናል የሚሉት ሀሰት ነው-- ዶክተር እንዳለ ኃይሌ

ሐምሌ 22 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ሀገራትን ጨምሮ የዓለም አቀፍ ተቋማትና ማህበረሰብ አይናቸው እያየ የሽብርተኛው ህወሃትን ድርጊት አለማውገዛቸው ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች ቆመናል ለሚሉት ሀሰት ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ አስታወቁ።

ዲሞክራሲ፣ ለሰብዓዊ መብቶችና ለዜጎች መብት በተግባር ሲቆሙ እንደማይታዩ የጠቆሙት፤ ዶክተር እንዳለ በታሪክ አሜሪካ ሰላም አሰፍናለሁ ብላ በገባችባቸው ሀገራት ሁሉም መፍረሳቸውን እና ከፍተኛ የሆነ የዜጎቸ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በስፋት መስተዋላቸውን አመልክተዋል።

የውጭ ኃይሎች ከዜጎች ሰብዓዊ መብት ጥሰት ይልቅ የሚያሳስባቸው የፖለቲካ ጥቅማቸውና ፖሊሲያቸውን የሚያስፈጽምላቸውን አሻንጉሊት መንግሥት መመስረት እንደሆነም ተናግረዋል።

እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናትን በውትድርና መልምሎ ማሰማራት በዓለም አቀፍ ህጎች የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው ያሉት ዶክተር እንዳለ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከዚህ በሚጻረር መልኩ ቢስተዋልም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት የሚከታተሉ ተቋማት በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ሲያወግዙ እንደማይስተዋሉ ገልጸዋል።

የዓለም አቀፍ ተቋማትና ማህበረሰብ አይናቸው እያየ ማውገዝ አለመቻላቸው እራሱ ሊወገዝ የሚገባው ጉዳይ ነው አሜሪካና የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች ቆመናል የሚሉት ሀሰት ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገባ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም