ቀጥታ፡

ፌዴራል ፖሊስ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ጋር ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ነው

ሐምሌ 22 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ጋር ልዩ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል።

የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ መስዋዕትነት እየከፈሉ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ተናግረዋል።

ውይይቱ ፖሊስ ሀገራዊ ተልዕኮውን ይበልጥ ማገዝ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደሆነ መገለጹን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም