ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ አሸባሪው ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ ድጋፍ የሚጠናከርበትን ውሳኔ አሳለፈ

ጋምቤላ ሐምሌ 21/2013 (ኢዜአ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሀገር ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ድጋፋቸወን የሚጠናከሩበትን የውሳኔ አሰለፈ።

ምክር ቤቱ አሸባሪው ቡድን ህፃናትንና አዛውንቶችን በመማገድ ሀገር ለማፍረስ የፈጸመውን ጥቃት በጽኑ አውግዟል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት የአሸባሪው ህወሓት ባለፈው 27 ዓመታት ጋምቤላን ጨምሮ በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ሳያንሳው አሁንም ሀገር ለማፍረስ ዘመቻ መክፈቱን ተናግረዋል።

ቡድኑ ሀገር ለማፍረስ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ የተጀመረውን ሕግ የማስከባር ዘመቻ በድል ለመቋጨት መላው ኢትዮጵያውን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰላፍ ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

የጋምቤላ ክልል ሕዝብና መንግሥትም ከሰራዊቱ ጎን የሚሰለፍ ልዩ ኃይል መላክን ጨምሮ የተለያየ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ለተጀመረው ሀገርን የማዳን ዘመቻ ስኬት የክልሉ ድጋፍ እንዲጠናከር ምክር ቤቱ የውሳኔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል።

ከምክር ቤቱ አባላት መካከል አቶ ሰናይ አኩዎር ፤  የህወሐት አሸባሪ ቡደን ህፃናትና አዛውንቶችን ለጦርነት በማሰለፍ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የከፈተው ጦርነት የሚወገዝና ሰይጣናዊ ድርጊት ነው ብለዋል።

ቡድኑ የጀመረውን ጦርነት ለመቀልበስ የክልሉ ሕዝበና መንግሥት ድጋፍና ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

ቡድኑ ጦርነት የከፈተው የኢትዮጵያን እድገትና ልማት የማይፈለጉ አንዳንድ የውጭ ሀገራትን በመወከል ጭምር መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላው የምክር ቤት አቶ አሸኔ አስተኒ ናቸው።

የቡድኑን ጥፋት ለማምከን አንድነትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ሌለው የምክር ቤት አባል ዶክተር ሉው ኡቡፕ በበኩላቸው፤ ጊዜው ከምንም በላይ የሀገርን ጉዳይ በማስቀደም አንድነት አጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል።

ምክር ቤቱ ሀገር ለማዳን በክልሉ መንግሥትና ሕዝብ የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲጠናከር በሙሉ ድምፅ መወሰኑን የኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት ከጋምቤላ ዘገቧል።   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም