የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል - ኢዜአ አማርኛ
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል
አዲስ አበባ ሃምሌ 21/2013(ኢዜአ) የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው እለት ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
የማዕከሉ አመራሮችና ሰራተኞች "ኢትዮጵያን እናልብሳት" በሚል መሪ ሃሳብ ነው በየካ ሚሊኒየም ፓርክ በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት፡፡
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና የማዕከሉ አመራሮችና ሰራተኞች ኢትዮጵያን እናልብሳት የሚለውን አገራዊ ጥሪ ተቀብለው አገር በቀል ችግኞችን መትከላቸውን ተናግረዋል፡፡
የተቋሙ ሰራተኞች በቀጣይ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ እንደሚያከናውኑም ነው የገለጹት።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የህዳሴ ግድብን ከደለል በመከላከል ረገድ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም በመርሃ ግብሩ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሻራቸውን ካሳረፉት የማዕከሉ ሰራተኞች መካከል አቶ ጀማል መሀመድ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንዲጸድቁ ተገቢውን እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ሁሉም በየአካባቢው ችግኝ በመትከል ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ሃላፊነቱን እንዲወጣም አስገንዝበዋል፡፡