በአሸባሪው ህወሃት የተቃጣውን አገርን የማፍረስ ሴራ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን እናሶግዳለን--የሰቆጣ ወጣቶች - ኢዜአ አማርኛ
በአሸባሪው ህወሃት የተቃጣውን አገርን የማፍረስ ሴራ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን እናሶግዳለን--የሰቆጣ ወጣቶች
ሰቆጣ ሐምሌ 20/201 (ኢዜአ) በአሸባሪው ህወሃት የተቃጣውን አገርን የማፍረስ ሴራ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ከማስወገድ የምናስቀድመው ምንም ነገር የለም ሲሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሰቆጣ ከተማ ወጣቶች ገለጹ።
ወጣቶቹ የክልሉ መንግስት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ በመቀበል ሃገርን ለማፍረስ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
የከተማው አንዳንድ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሰጡት አስተያየት ዓዋጁ ሽብርተኛውን ህወሃትን በመደምሰስ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነትን ያስጠብቃል። ዘላቂ ሰላምን ያረጋግጣል።
የከተማው ነዋሪ ወጣት አበባው ቴዎድሮስ ''የክተት ጥሪ በመቀበል ራሴን ለህልውና ዘመቻ አዘጋጅቻለሁ'' በማለት ጥሪው የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት ያስጠብቃል የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።
በዚህም የአሸባሪውን ቡድን ተስፋ ለማጨለምም በቁጭት መነሳቱን ገልጾ “እኛ ወጣቶች እንደ አባቶቻችን የአገርን ዳር ድንበር በማስከበር አንድነቷን የማስቀጠል አደራ አለብን'' ሲልም
ወጣት ሲሳይ አጥናፌ በበኩሉ በዙ ዘመን በሃገር ህልውና ላይ የተቃጣውን ጥቃት ለመመከት የክተት ዓዋጁን በመቀበል የሚፈለግበትን ግዳጅ ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታውቋል።
ጁንታው በአማራ ሕዝብና በኢትዮጵያ ደህንነት ላይ የደቀነውን አደጋ ለማክሸፍ እንደሚሰማራም አረጋግጧል።
‘'እኔ ያልመራኋት አገር ትፍረስ' የሚለውን የአሸባሪው ህወሃት አሸባሪ ቡድን ቆመን አናይም'' የሚለው ወጣት ሲሳይ፣ የአባቶችንን አደራ ጠብቆ ታሪክ ለመሥራት መዘጋጀቱን ገልጿል።
“ለዕኩይ ተግባሩ ማስፈጸሚያ ሕጻናትን ለጦርነት በመማገድ ሃገር ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ቡድን በመደምሰስ ከሌሎች ወጣቶች ጋር ታሪክ እንሰራለን” ብሏል።
“የጁንታውን እኩይ ተግባር ለመመከት ከተሰለፈው ሕዝብ ጎን ቆሜያለሁ” ያለው ደግሞ ወጣት ፍቅሩ ኃይሉ የተባለው የከተማው ወጣት ነው።
“የክልሉ መንግሥት ያቀረበውን የክተት ጥሪ በመቀበልም እዘምታለሁ” ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷተል።
የሰቆጣ ከተማና አካባቢዋ ወጣቶች የክተት ዓዋጁን ተከትሎ በአገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሺያነት ለመሳተፍ እየተመዘገቡ መሆናቸውን መረጃዎቹ ያመለክታሉ።