ቀጥታ፡

የአለም ኢኮኖሚ 6 በመቶ እንደሚያድግ አይኤም ኤፍ አስታወቀ

ሀምሌ 20/2013 (ኢዜአ) እ.ኤ.አ በ2021 የአለም ኢኮኖሚ 6 በመቶ እድገት እንደሚያሳይ የአለም የገንዘብ ደርጅት (አይ ኤም ኤፍ) አስታወቀ።

አይ ኤም ኤፍ 2021 የአለም ምጣኔ ሃብት እድገትን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት የዚህ ዓመት የኢኮኖሚ እድገት ከዚህ ቀድም በሚያዝያ ወር ከተተነበየው ጋር ተመሳሰይ ሆኖ ታይቷል ብሏል።

በዚህም የአለም ኢኮኖሚ ወደ ስምንተኛ ወሩ በቀረበው 2021 ስድስት በመቶ እድገት እንደሚያሳይ አስታውቋል።

በሌላ በኩል የቻይና ኢኮኖሚ 8.1 በመቶ እንደሚያድግ በሪፖርቱ መጠቆሙን ያመለከተው ሲጂቲኤን ከሚያዝያ ውር ጋር ሲነጻጸር 0.3 በመቶ ዝቅ ማለቱን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም