ቀጥታ፡

ህወሃት ሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተሽከርካሪዎች ለህዝቡ እንዳያደርሱ እንቅፋት ሆኗል--ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

ሀምሌ 20/2013 (ኢዜአ) ህወሃት ሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተሽከርካሪዎች ለህዝቡ እንዳያደርሱ እንቅፋት መሆኑን ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገለፀ።

መንግስት የሰብአዊ ዕርዳታ እንዲደርስ ለማስቻል አልሞ ያደረገው የተናጠል የተኩስ አቁም በሕወሃት ትንኮሳ መደናቀፉን ቀጥሏል።

መንግስት ትግራይን ለቆ ከመውጣቱ በፊት በትግራይ ክልል በሚገኙ መጋዘኖች ከ400 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስንዴ እና ከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የሚበልጥ የምግብ ዘይት አስቀምጧል፡፡

የትግራይ ህዝብ ደህንነት የኢትዮጵያን መንግሥት እንደሚያሳስበው ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል።

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያው እንዳለው ዓለም አቀፍ ተቋማት በተለይ በትግራይ ክልል በስራ ላይ ያሉ ተቋማት ህወሃት የአፋርን ክልል መተናኮሱን አቁሞ ሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተሽከርካሪዎች ድጋፎችን ለህዝቡ እንዲያደርሱ ግፊት ማሳደር እንዳለባቸው አስታውቋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም