ቀጥታ፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድንን ለመመከት ከሀገር መከላከያ ጎን እንደሚሰለፉ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

ጋምቤላ ፤ ሐምሌ 19/2013(ኢዜአ) ሀገር ለማፈረስ እየጣረ ያለው አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በመመከት ሴራውን ለማክሸፍ ከሀገር መከላከያና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጎን እንደሚሰለፉ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የከተማዋና አካባቢው ነዋሪዎች የጥፋት ቡድኑን በማውገዝና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት  ደጀንነታቸውን ለመግለጽ ዛሬ በጋምቤላ  ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄደዋል።

ከሰልፈኞቹ መካከል መቶ አለቃ ኡጁሉ ቻም በተለይ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ የህወሓት ጁንታ ባለፉት  27 ዓመታት ህዝቦች ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ሳይበቃው አሁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየጣረ  መሆኑ እንዳስቆጣቸው ገልጸዋል።

ቡድኑ በሀገር ላይ የከፈተውን ጥቃት ለመቀልበስ ከሀገር መከላከያና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጎን ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

አሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሸረበውን ሴራ ለማክሸፍ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሊቆሙ ይገባል ያሉት ደግሞ ሌላው ከተማዋ ነዋሪና የሰልፉ ተሳታፊ የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ አመራር አቶ ዘሪሁን በየነ ናቸው።

የጁንታውን የጥፋት ድርጊት በመመከት ለማክሸፍ የፖለቲካ ልዩነቶችን በመታው በጋራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ፤ የቡድን ሴራ ለመቀልበስ የህይወት መስዋዕትነት ለመክፍል ጭምር ዝግጁ መሆናቸውን  ገልጸዋል።

 አቶ ጋዴት ሩይ በበኩላቸው፤  የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ደጋም በኢትዮጵያ ላይ ዘረፋ፣ በህዝቦች ላይ ግፍና በደል እንዲጽም አንፈቅድም ብለዋል።

ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን በማጠናከር የኢትየጵያ ነቀርሳ የሆነውን የህወሓት ቡድን ነቅሎ ለመጣል በተባበር ክንድ ሊመክት ይገባል  ያሉት ደግሞ ሌላው የሰልፉ ተሳተፋ አቶ ዓለማየሁ ቦጋለ ናቸው።

የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ወጣት ኡችዎድ ባች ለሰልፈኞቹ ባደረገው ንግግር፤ የክልሉ ወጣቶች የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን ሀገር ለማፈረስ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልባስ የክልሉ ወጣቶች ዝግጁ መሆናቸውን  አስታውቋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፤ በበኩላቸው፤ የጥፋት ቡድኑ በሀገር ላይ የሰነዘረውን ጥቃት  ለመቀልበስ ለተጀመረው ዘመቻ ስኬት የክልሉ ህዝብና መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀዋል።

ህፃናትን ለጦርነት ማሰለፍ በዓለም ዓቀፍ ህግ የተከለከለ መሆኑ እየታወቀ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አንዳንድ ሀገራት አይታው እንዳላዩ ዝም ማለታቸው ኢትጵያን ለማዳካም የተጠነሰሰ ሴራ መሆኑን እንደሚያሳይ  ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን  ለማዳከማ ከውጭም ሆነ ከውስጥ የተጠነሰሰው ሴራ በጀግኖች ልጆቿ ክንቱ እንደሚቀርም ርዕሰ መስተዳደሩ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ነው፣ ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቅም፤ ግድባችንን እንደጀመርነው እንጨርሰዋልን የሚሉና ሌሎችን መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ የከተማዋ አካባቢው ወጣቶችና ሴቶች ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  ሪፖርተር ከጋምቤላ ዘግቧል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም