አሸባሪው ህወሃትን የሚቃወም ሰልፍ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪው ህወሃትን የሚቃወም ሰልፍ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው
አሶሳ ፤ ሐምሌ 19/2013(ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪው ህወሃትን በማውገዝና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
ነዋሪዎቹ እያካሄዱት ባለው ሰላማዊ ሰልፍ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አልኝታችን ነው፣ ለሀገራችን አንድነት ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን እንቆማለን ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ ግንባታ ከመጨረስ የሚያግደን አንዳችም ምድራዊ ሃይል የለም የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች እያስተላለፉ ነው።
በሰላማዊ ሰልፉ ከአሶሳ ከተማና አካባቢዋ የተሰባሰቡ ብዛት ያላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡