ቀጥታ፡

የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

ጋምቤላ፤ ሐምሌ 19/2013(ኢዜአ) የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና አሸባሪው ህወሃትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

ሰልፈኞቹ አሸባሪው የህወሃት ጁንታ የመላው ኢትዮጵያ ጠላት ነው፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከፍጻሜ ለማደረስ እንሰራለን፣ የዘመኑ ትውልድ ኢትዮጵያን የመጠበቅ  የአባቶቹ አደራ ይወጣል የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

ነዋሪዎቹ በከተማዋ ጎዳናዎች በመዘዋወር  ድምጻቸውን ካሰሙ በኋላ  ወደ ጋምቤላ ስታዲየም በማምራት ተሰባስበው መልዕክት እያስተላለፉ ነው።

በሰላማዊ ሰልፍ ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም