ቀጥታ፡

በአፋር የተለያዩ ከተማች የህወሃት ሽብር ቡድንን የሚያወግዝና መከላከያን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

ሰመራ፣ ሀምሌ 18 /2013 (ኢዜአ) በአፋር ክልል የተለያዩ ከተማች የህወሃት ሽብር ቡድንን የሚያወግዝና መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂደ።

ሰልፉ አሳኢታና ሠመራ-ሎግያን ጨምሮ በክልሉ በተለያዩ ከተሞች ዛሬ ተካሂዷል።

በተለይም በሰመራና አሳኢታ ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች ነዋሪዎች በውጭ ጣልቃ ገብነት የታገዘ የህወሃት የሽብር ቡድን በአፋር ንጹሃን አርብቶ አደሮች ላይ ያደረሰውን ጥቃት አውግዘዋል ።

ሰልኞቹ ቡድኑ አፋርን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጽመውን  የዘር ማጥፋት ወንጀል ኮንነዋል።

ከመከላከያ ሰራዊትና የክልሎች የጸጥታ ሃይሎች እንዲሁም  ከመንግስት ጎን በመቆም አሸባሪውን ህወሀት እንደሚፋለሙ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።

የትግራይ ህዝብ ወገናችንና አንዱ የኢትዮጵያ አካል መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ  "ወያኔ ፍላጎቱን በጉልበት ሊጭንብን አይገባም" ሲሉ አውግዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም