የጎንደር ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኃይልና ለሚሊሻው አጋርነታቸውን በሰልፍ እየገለጹ ነው

45

ጎንደር ሀምሌ 18/2013 ( ኢዜአ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለልዩ ኃይልና ለሚሊሻው ያላቸውን ሕዝባዊ አጋርነት በሰልፍ እየገለጹ ነው።

በከተማው መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ ከተለያዩ ክፍለ  ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባት አርበኞች የከተማው  የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እየተሳተፉ ናቸው።

ነዋሪዎቹ እኛነታችንን አናስከብራለን፣ ኢትዮጵያን ሊቀብሯት የተነሱትን ሁሉ በመቅበር ሁሌም አሸናፊ ነን፣ የአማራ ጀግኖች ሰማዕታት የእኛ የትግል ሥንቅ ናቸው፣ መከላከያ  ሠራዊታችን የሉአላዊነት ምልክት ነው፣ የህዋሃት ጁንታ ቡድን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ነው የሚሉና መሰል መፈክሮችን በማስተጋባት ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም