የአሸባሪው ህወሀት የጥፋት ተግባር ለመቀልበስ የክልሉ ህዝብ ልጆቹን መርቆ እየላከ ነው --- ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ

66

ሀዋሳ፣ ሐምሌ 17/2013 (ኢዜአ.) የአሸባሪው ህወሀት የጥፋት ተግባር ለመቀልበስ የክልሉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ለሀገር አሌኝታ ለሆነው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ ልጆቹን መርቆ እየላከ ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ።

ሁለተኛው ዙር የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል የፖሊስ አባላት ወደ ግዳጅ ለመሰማራት በሀዋሳ የቀድሞ ስታዲዮም የሽኝት መርሀ ግብር ማምሻውን በተካሄደበት ወቅት  ርዕስ መስተዳደሩ እንዳሉት፤  የጁንታው አስተዳደር ያማረራቸው የሀገሪቱ ህዝቦች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከስልጣን አባረውታል።


ሆኖም ብዛበዛና ጥቅም ስለቀረበት ሀገሪቱን በማተራመስ ወደ ስልጣን ለመመለስ በመቋመጥ ሰራዊታችንን ከጀርባ በመውጋት ሰፊውን ህዝብ አሰቆጥቷል ብለዋል።


በድርጊቱ የተቆጨው ህዝብ በትግራይ ክልል የተካሄደውን ህግ ማስከበር ዘመቻ በመደገፍ በአጭር ግዜ ተልኮውን ለማሳካት መቻሉን ጠቅሰዋል።


ይህንን ተከትሎ መንግስት በትግራይ ክልል ሰብአዊ ቀውስ እንዳይባባስና መንግስታዊ አገልግሎት ህዝቡ አግኝቶ ፊቱን ወደ ልማት እንዲመልስና የጥሞና ጊዜ እንደያገኝ የተናጥል ተኩስ በማቆም ህዝባዊነቱን አረጋግጧል ብለዋል።


ሆኖም  ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ጥሌ ከአማራ ህዝብ ጋር ነው በማለት የሀሰት ፖሮፖጋንዳ በመንዛትና ህዝቡን በመከፋፈል የስልጣን ጥሟቱን ለመወጣት ዳግም ጦርነት መክፈቱን አመልክተዋል።


የተከፈተው ጦርነት የአንድ ክልል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ይልቁንስ ሀገር የማፍረስና የማዋረድ ሴራ እንደሆነ አስታውቀዋል።


ይህንን የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ተግባር ለመቀልበስ የክልሉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ለሀገር አሌኝታ ለሆነው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ ልጆቹን መርቆ እየላከ ነው ብለዋል።


የክልሉ መንግስትም ምንም ዓይነት የሀይል አሰላለፍ ክፍተት እንዳይፈጠር ለማድረግ ተጨማሪ ሀይል ዛሬ ማሰማራቱን ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ጎናቸው በመሆን ያልተቆጠበ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።


የክልሉ የመንግስት ሰራተኞችም ለሰራዊቱ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከመለገስ ባለፈ በግንባር ለመሰለፍ የመንግስትን ጥሪ እየጠበቁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።


የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በበኩላቸው፤ የመንግስትን ጥሪ ተቀብላችሁ ለመዝመት በመወሰናችሁ ቆራጥና ጀግኖች ስለሆናችሁ ክብር ይገባችኋል ብለዋል።


ዘማቾቹ   በበኩላቸው ተንበርክከው ለተረከቡት ሰንደቅ ዓላማ ሲሉ ወቅቱ የሚጠይቀውን መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም