ቀጥታ፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ድጋፉን እንደሚቀጥል ገለጹ

ጅማ፣ ሐምሌ 16/2013 (ኢዜአ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ገለጸ።
በግድቡ ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በተወያዩበት ወቅት እንደተመለከተው፤  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተቋሙ ማህበረሰብ የአንድ ወር ደመወዙን ቦንድ በመግዛት ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ  ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ትልቅ ድል መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው የያዘችው አቋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው ተናግረዋል።

ግብፅና ሱዳን የውሃ ሙሌቱ በተያዘለት ጊዜ እንዳይከናወን ብዙ ርቀት ቢጓዙም በተከናወነው  ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ሴራዋ መፍረስ በመቻሉ ዲፕሎማቶቻችንን ያስመሰግናቸዋል ብለዋል።

የተገኘው የዲፕሎማሲ ውጤት የኢትዮጵያን የመደራደር አቅምና እውነታ ዳግም ለአለም ያረጋገጠ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ጴጥሮስ፤ የተገኘው ዲፕሎማሲያዊ ድል ቀጣይነት እንዲኖረው መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ቢዝነስና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ካሳሁን ወዳጆ በበኩላቸው፤ ተቋሙ የግድቡን ግንባታ ሲደግፍ መቆየቱን አስታውሰው፤ "ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድጋፋ ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት አመት የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የአንድ ወር ደመወዙን ቦንድ በመግዛት ከ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም