ቀጥታ፡

በደቡብ ክልል ሁለተኛው ዙር የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት የሽኝት ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ ፤ ሐምሌ 15 ቀን 2013 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል 2ኛ ዙር የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን ወደ ግዳጅ ቀጠና ለማሰማራት የሽኝት ሥነ-ሥርዓት በሀዋሳ የቀድሞ ሁለገብ ስታዲየም እየተካሄደ ነው።

በአሁኑ ወቅት ሽኝት እየተደረገላቸው የሚገኙት የልዩ ኃይል አባላት ዝግጁነታቸውን የሚያስመሰክር ትርኢት እያቀረቡ ይገኛሉ።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የጸጥታ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም