ኢዜማ በ28 ምርጫ ክልሎች ላይ ያለውን አቤቱታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አስገባ - ኢዜአ አማርኛ
ኢዜማ በ28 ምርጫ ክልሎች ላይ ያለውን አቤቱታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አስገባ
ሐምሌ 15 / 2013( ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ በ28 ምርጫ ክልሎች ላይ ያለውን አቤቱታ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ማስገባቱን ገለፀ።
ፓርቲው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፤ በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በተካሔደባቸው 28 የምርጫ ክልሎች ላይ ያለውን ቅሬታ መሰረት አድርጎ ምርጫ እንዲደገም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስገብቷል።
ፓርቲው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እነዚህን ምርጫ ክልሎች በተመለከተ የቀረቡለትን “ቅሬታዎች እና ማስረጃዎች ሳይገመግም ውሳኔ በማስተላለፉ ነው" በሚል መሆኑን አስታውቋል።
ፓርቲው ምርጫው እንዲደገም አቤቱታ ካቀረበባቸው 28 ክልሎች መካከል 27ቱ በደቡብ ክልል የሚገኙ ሲሆን፤ አንዱ ደግሞ በጋምቤላ ክልል መሆኑን ገልጿል።