ጁንታው የህወሓት ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋለጠ - ኢዜአ አማርኛ
ጁንታው የህወሓት ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋለጠ

ሐምሌ 15 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሸባሪውና ጁንታው የህወሓት ቡድን የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ መጋለጡን የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የሽብር ቡድኑ በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን በሚያስገባቸው ሠርጎ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ታውቋል።
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ እንደገለጸው ይሄንን ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ልዩ ኃይልን ትኩረት ለማዛባት ሞክሯል።
የጦር ኃይሉን ወደ ራያና አፋር ሲሰባሰብና የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በዚያ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን ያሳያል ብሏል መረጃ ማጣሪያው።
ጁንታው ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል ሲል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ማስጠንቀቂያ 1 በሚል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።