የመዲናዋ ነዋሪዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር እየተወያዩ ነው

56

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2013(ኢዜአ) የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይና የአገር መከላከያ ሠራዊቱን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ነው።

"ክብር ለመከላከያ ሠራዊታችን" በሚል እየተካሄደ ባለው ውይይት የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላትና ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ሠራዊቱ ጠንካራ የሕዝብ ደጀን ያለው መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ በመሆኑም ሠራዊቱ እንኳን ለኢትዮጵያ ሀገሩ ለሌሎችም ድል እያስገኘ መቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡

ውይይቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለአገር መከላከያ ሠራዊት እያደረጉት ያለውን ሕዝባዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም