ለጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች አገር አቀፍ የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ለጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች አገር አቀፍ የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር እየተካሄደ ነው
62
ሐምሌ 11 ቀን 2013 (ኢዜአ) ለጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች አገር አቀፍ የእውቅናና ምስጋና መረሃ-ግብር በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።
በመረሃ-ገብሩ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
መረሃ-ግብሩ በዋናነት የተዘጋጀው በተለይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች መሆኑን ተገልጿል።
ዛሬ የተጀመረው አገር አቀፍ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ተጠቁሟል።