ቀጥታ፡

የሃረሪ ፖሊስ የህወሃት የሽብር ቡድንን የጥፋት ተልዕኮ ለመከላከል ወደ ስፍራው ሊያቀና ነው

ሐረር፤ሐምሌ 10/2013 (ኢዜአ) የሃረሪ ክልል ፖሊስ የህወሃት የሽብር ቡድንን የጥፋት ተልዕኮ ለመመከት በሚደረገው ትግል ላይ ለመሳተፍ ሽኝት እየተደረገለት ነው።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነስሪ ዘካሪያ ለኢዜአ እንደገለጹት የፖሊስ አባላቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ሃገር ለማፍረስ የሚያደርገውን ዘመቻ ለመቀልበስ ነገ ወደ ግዳጅ ቀጠናው በማምራት ከሌሎች አጋሮቹ ጋር ይቀላቀላል።

“መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰላምና መረጋጋት በማሰብ በሰጠው የጥሞና ጊዜ የተናጥል የተኩስ አቁም ቢያደርግም የጥፋት ሃይሉ ከችግር ፈጣሪነቱ አልተቆጠበም”ብለዋል።

በዚህም አሸባሪው ሃይል ሃገር ለማፍረስ የጀመረውን ዘመቻ ለመቀልበስ የፖሊስ አባላቱ ከሌሎች የኢትዮጵያ "የቁርጥ ቀን ልጆች" ጋር በመሆን ግዳጁን በጀግንነት እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

በሐረር በሚገኘው መኮንኖች ክበብ አዳራሽ ማምሻውን በተዘጋጀው የሽኝት መርሃ-ግብር ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር፣የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም