የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመተባበር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመተባበር ተስማሙ
ሀምሌ 10/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰላምና ልማት ዙሪያ ለመተባበር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ።
በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ የተመራ ልዑክ ከኬንያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሊቀመንበር ቢሾብ ጆሰፍ ማታው ጋር ባደረጉት ውይይት በሰላምና ልማት ዙሪያ ለመተባበር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ችለዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑካን ቡድን በናይሮቢ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን የእምነት ተቋማት ተወካዮች ጋር ዛሬ በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውይይትማድረጋቸው ተጠቁመዋል።
በናይሮቢ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቅርንጫፍ ለመመስረት አደራጅ ኮሚቴ መሰየሙም ተነግሯል፡፡