ቀጥታ፡

የአረፋን በዓል ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳትና ለኢትዮጵያ አንድነትና አብሮነት "ዱአ" በማድረግ መሆን አለበት- ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ

ሀምሌ 10/2013 (ኢዜአ) የአረፋን በዓል ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና ለኢትዮጵያ አንድነትና አብሮነት "ዱአ" በማድረግ መሆን አለበት ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ ገለጹ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ ለአረፋ (ኢደል አደሃ) በዓል ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ለኢትዮጵያ አንድነትና አብሮነት "ዱአ" በማድረግ መሆን አለበት ብለዋል።

የአረፋ በዓል እርድ የሚከናወንበት ለጎረቤትና የተቸገሩ ወገኖች በማካፈል የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል። 

ህዝበ ሙስሊሙ የበዓሉን አከባበር ስርአት ተከትሎ በማከናወን ማክበር እንዳለበትም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።

የኢደል አደሃ (ዓረፋ) በዓል በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ይከበራል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም