የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ
ሐምሌ 10/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 476 የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ።
ሠልጣኞቹም በፖሊሰ ሳይንስ፣ በስነ-ወንጀልና ወንጀል ፍትህ፣ በነርሲንግ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ዩንቨርስቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችንም አስመርቋል።
በየትምህርት ዘርፉ የላቀ ውጤት ላመጡ ተመራቂ መኮንኖች ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ዩንቨርስቲው ከተቋቋመ 74 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በቅርቡም ከኮሌጅ ወደ ዩንቨርስቲ ማደጉ ይታወሳል።
በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተካሄደ የምርቃት ስነ-ሰርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ተገኝተዋል።