ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቸን እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቸን እያስመረቀ ነው
ባህር ዳር ፤ ሐምሌ 10/2013 (ኢዜአ) ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መሰኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 356 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክና ኮሙዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘውዱ እመሩ ተናግረዋል።
ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 726 ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንሰና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።