ቀጥታ፡

አሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ልታደርግ ነው

አሜሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ሐምሌ 09 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሜሪካ 453 ሺህ 600 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ።

በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ክትባት "ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን" የተባለው ክትባት ሲሆን የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ርክክብ ይደረጋል ተብሏል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የአሜሪካ አምባሳደር በተገኙበት ርክክቡ የሚከናወን እንደሆነም ታውቋል።

አሜሪካ በሚቀጥሉት ሳምንታት 25 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ለ49 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ የምትለግስ መሆኑን "ጋቪ" በተሰኘ ዓለም አቀፍ ክትባት አቅራቢ ተቋም ባወጣው መረጃ አመላክቷል።  

በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ አንድ ሚሊዮን ዶዝ ክትባት ለቡርኪና ፋሶ፣ ለጂቡቲ እና ኢትዮጵያ ተደራሽ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ቫይረሱን ለመከላከል እስካሁን ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች "የአስትራዘኒክ" እና "ሲኖፋርም" ክትባቶችን መስጠቷ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም