የአገር መከላከያ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት የወቅታዊ ሁኔታ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች - ኢዜአ አማርኛ
የአገር መከላከያ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በሰጡት የወቅታዊ ሁኔታ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች
- ጁንታውና የጁንታው ውጫዊ ሃይል (ገዢዎቻቸው) የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ትንኮሳዎችን በማድረግ እኛ ለጥበቃ፣ ለሳተላይት ያስቀመጥናቸውን አሃዶች፣ የክልል የጸጥታ ሃይሎችን ማጥቃት እንደ እንድ ምቹ አጋጣሚ ተጠቅመው እየሰሩ ነው፣
- ድሮም ኮረምና አላማጣ አካባቢ ሰራዊት አልነበረንም፤ ነገር ግን ሃይል ማስቀመጥ ስለነበረብን የተቀመጡትን የመከላከያና የአካባቢ ሃይሎች የወያኔ ገዢዎችና ጁንታው አጋጣሚውን በመጠቀም ሃይላችንን አጥቅቶ ለመደምሰስ ሙከራ አድርጓል፣
- ከህዝብ ጋር አንዋጋም ህዝቡም ይረስ በሚል የተናጠል ተኩስ አቁም ተደርጓል፣
- ከማዕከላይ ትግራይ ሲቪሎችን አንቀሳቅሶ መሳሪያ፣ ንብረትና ገንዘብ ታገኛላቹ በሚል አሰማርቷል፣
- ባለፉት ጊዜያት የጁንታው ቡድን የነበሩትን ባህሪ ካየን በግጭት ውስጥ የኖረ ቡድን በመሆኑ ምንጊዜም ግጭት ለቡድኑ መፋፊያ ማደጊያ በመሆኑ የተናጠል የተኩስ አቁሙን አይቀበልም፣
- ትንኮሳ ዋነኛ ባህሪው የሆነው ወያኔ ግጭት ውስጥ ለመኖር በተለያዩ አጋጣሚዎች ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብና የዓለም ማህበረሰብ እንዳየው ቡድኑ ያሰማራቸው ወይም የመለመላቸው የ14፣ የ15 ዓመት ልጆች ናቸው፣
- እነዚህ ልጆች ናቸው ጠመንጃ ይዘው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና ከአካባቢ የጸጥታ ሃይሎች ጋር እንዲዋጉ ያዘመቷቸው፣
- ወያኔ የተኩስ አቁም ውሳኔውን የማይቀበልበት ሌላው ምክንያት ከትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ጥያቄ ስለሚቀርብበትና ምናልባትም መቀበሪያውና ከህዝብ የሚነጥለው በመሆኑ አለመቀበልና ትንኮሳውን እንዲቀጥልበት ገፋፍቶታል፣
- ወታደራዊ ስራዎች የሚከናወነው በወታደሮች ብቻ እንጂ በአክቲቪስቶች የሚከናወን አይደለም፣
- ኢትዮጵያን የመበተን የወያኔ ፍላጎት የማይሳካ መሆኑን ማሳየት ብቻ ሳይሆን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉንም ሃይላችንን በመጠቀም የት ቦታ፣ መቼ ማጥቃት አለብን የሚለው ነገር ላይ በሚገባ እየሰራን እንገኛለን፣
- የወያኔን ጊዜያዊ ፉከራ በመስማት ለእሱ ሰለባ መሆን አያስፈልግም፣
- መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰራዊታችን ጎን ሊሰለፍ ይገባል። በሰው ሃይል፣ በቁሳቁስና በሞራል ከሰራዊታችን ጎን መቆም ያስፈልጋል፣
- እኛ ስንናገርም ስንሰራም ሃላፊነት ያለብን የአገር መከላከያ ሰራዊት አባል ነን፤ ወያኔ የመከላከያ ሰራዊትንም ሆነ መንግስትን ለመወንጀል እውነትን መፈለግ የለበትም የሚፈለገውን ነገር መፈብረክ አለብን ብለው እየሰሩ ነው፣
- እነሱ ውሸት ቢናገሩም ተጠያቂነት የሌለባቸው በየበረሃው የሚንቀሳቀስና የሚያስተዳድረው ቦታ የሌለው ነው፤ እኛ የምናስተዳድረው አገር አለን፣
- መስዋዕትነንት ከፍለን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል እየሰራን ነው።