በአዲስ አበባ ከ900 በላይ ለሆኑ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ ተደረገ

97

ሐምሌ 06 ቀን 2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ከ900 በላይ ለሆኑ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ ተደረገ።

ለአርሶ አደሮቹ ድጋፍ ያደረገው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክፍለ ከተማ የ2013/14 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ያዘጋጀ ሲሆን ለአርሶ አደሮችና መስራት ለማይችሉ አቅመ ደካሞች የተለያዩ ድጋፎችንም አበርክቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ለ934 የከተማ አርሶ አደሮች የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ድጋፍ ሲያደርግ ለ290 አቅመ ደካሞች ደግሞ ብርድ ልብስና አንሶላ አበርክቷል።

የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን አምባዬ በመዲናዋ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች የመሬት ማረጋገጫ ደብተር እየተሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል።

"በመሆኑም አርሶ አደሩ መሬቱን ከመሸጥ ይልቅ በመሬቱ ላይ ሰርቶ እንዲጠቀም በማሳሰብ በኢኮኖሚ ራስን ለመቻል ሁላችንም መታገል አለብን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የዘንድሮውን የመኸር እርሻ ስራ በይፋ ማስጀመሩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም