ቻይና በኢትዮጵያ የተሳካ ምርጫ መካሄዱን አስመልክታ የ’እንኳን ደስ አላችሁ’ መልዕክት አስተላለፈች - ኢዜአ አማርኛ
ቻይና በኢትዮጵያ የተሳካ ምርጫ መካሄዱን አስመልክታ የ’እንኳን ደስ አላችሁ’ መልዕክት አስተላለፈች
ሐምሌ 05 ቀን 2013 (ኢዜአ) ቻይና በኢትዮጵያ የተሳካ ምርጫ መካሄዱን አስመልክታ የ’እንኳን ደስ አላችሁ’ መልዕክት አስተላለፈች።
በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ለኢዜአ በላከው መግለጫ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በገለጸው ውጤት መሰረት በዶክተር አቢይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና ፓርቲ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ወንበር ማግኘቱን አስታውሷል።
ቻይና ምርጫው በስኬት በመጠናቀቁ የተሰማትን መልካም ምኞት ‘እንኳን ድስ አላችሁ’ ስትል ገልጻለች።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካሉ የቻይና ስትራተጂክ አጋሮች ዋናዋ መሆኗን ያመለከተው መግለጫው፤ የቻይና አፍሪካ ትብብር ፍሬ እንዲያፈራ የኢትዮጵያ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አመልክቷል።
የሁለትዮሽ ትብብሩ ተጠናክሮ ቀጥሎ ለህዝቡ የተሻለ ጥቅም እንደሚያስገኝም የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊጂያን ዣኦ መግለጻቸውን ኤምባሲው ጠቁሟል።