በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ዘርፍ የበጎ ፈቃድ አገልገሎት መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ዘርፍ የበጎ ፈቃድ አገልገሎት መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ
ሀምሌ 4/2013 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል የትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቢሾፍቱ ከተማ በመገኘት የመዋለ ህፃናት ትምህርት ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ አስጀምረዋል።
በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በኦሮሚያ ክልል 3 ሺህ የመዋእለ ህፃናት ትምርት ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን ገልጸዋል።
ለዚህም አስካሁን 13 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የጠቀሱት አቶ ሽመልስ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ህፃናት የመማር እድል እንዲያገኙና ከታች ጀምሮ በመስራት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት በክልሉ በተከናወነው ተመሳሳይ ተግባር 34 ሺህ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውንም አስታውሰዋል።
በትምህርት ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ኦሮሚያ ክልል በዘርፉ እያከናወነው ያለውን ተግባር ለሌሎችም መልካም ተሞክሮ መሆኑን ጠቅሰዋል።