ቀጥታ፡

የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ

ሀምሌ 3 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ምክር ቤቶች የምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።

ቦርዱ ዛሬ ሃምሌ 3 ቀን  2013 ዓ.ም የስድስተኛው አገራዊ የምርጫ ውጤት በአዲስ አባባ ይፋ አድርጓል።

በመድረኩም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ጨምሮ በምርጫው የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የሲቪክ ማህበራት ታድመዋል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ፣ የክልል ምክር ቤቶችን የምርጫ ወጤት ይፋ አድርጓል።

አዲስ አበባ  

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 138

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 10

ብልጽግና ፓርቲ ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 138

ድጋሚ ምርጫና ቆጠራ የሚካሄድባቸው የምርጫ ክልል የለም።

አማራ ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ - 294

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 125

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 128

አብን ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 13

ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት - 5

አፋር ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ - 96

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 25

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት 51

የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲ ድርጅት የመቀመጫ ብዛት - 3

ድጋሚ ቆጠራ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት - 5

ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት - 1

ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 99

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 6

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 22

ድጋሚ ቆጠራ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት - 1

ድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የምርጫ ክልል ብዛት - 1

ድሬዳዋ ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 189

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 47

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 189

ጋምቤላ ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 156

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 14

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 149

ጋህነን ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 7

ኦሮሚያ ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 537

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 171

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 513

ሲዳማ ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 190

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 19

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 190

ደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል

ክልሉ ያለው የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ብዛት - 291

ሰኔ 14 ቀን ምርጫው የተከናወነበት የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልል ብዛት - 89

ብልጽግና ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 245

ኢዜማ ያገኘው መቀመጫ ብዛት - 10

የጌዲኦ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ፓርቲ ያገኘው መቀመጫ  ብዛት - 6

ድጋሚ ቆጠራ የሚከናወንበት ምርጫ ክልል ብዛት - 3

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም