ቀጥታ፡

የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ16ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 157 እጩ መምህራንን አስመረቀ

ሃምሌ 3፤2013 (ኢዜአ)በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ16ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን አንድ ሺህ 157 እጩ መምህራንን አስመረቀ።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም የኃማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

የኮሌጅ ዲን ኮማንደር ጋዎ በበኩላቸው የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ-ኃይል በዞኑ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በመፍታት የትምህርት ሂደቱ እንዲቀጥል ጉልህ ድርሻ ማበርከቱን ተናግረዋል።

ኮሌጁ በጉሙዝኛ፣ ሽናሻኛ፣ በርትኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ትምህርት መስክ ስልጠና በመስጠት በክልሉ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም ነው የገለጹት።

ተመራቂዎቹ ሀገራቸውን በቅንነትና ታማኝነት እንዲያገለግሉም የኮሌጁ ዲን ጥሪ አቅርበዋል።የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ፣ በማታና በክረምት መርሃ-ግብሮች መምህራንን በማሰልጠን ለክልሉ ትምህርት ተደራሽነት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም