ቀጥታ፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 3 /2013( ኢዜአ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በየካ ክፍለ ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ ችግኝ ተከሉ፡፡

“ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለዴሞክራሲ ግንባታ ለሀገራዊና ህዝባዊ አጀንዳዎች በጋራ ይሰራሉ” በሚል አባላት ዛሬ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በባላንጣነት የሚተያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን ላይ በሀገራዊ ጉዳዮች በጋራ በመስራት አዲስ የፖለቲካ ባህል እየተፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ብልፅግና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለስ አለሙ ተናግረዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፌ በበኩላቸው ተሸናፊም ሆነ አሸነፊ ፖርቲ እንዲህ ባለ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡(ኢብኮ)

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም