የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ውጤታማ ዲፕሎማሲ የታየበት ነበር ... አምባሳደር ዲና ሙፍቲ - ኢዜአ አማርኛ
የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ውጤታማ ዲፕሎማሲ የታየበት ነበር ... አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
አዲስ አበባ፤ ሀምሌ 2/2013 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ውጤታማ ዲፕሎማሲ የታየበት ነበር ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫ አበይት ፖለቲካዊ ፣ ምጣኔ ሀብታዊና የዜጋ ዲፕሎማሲ ክንውኖችን አንስተዋል።
በትናንትናው ዕለት በፀጥታው ምክር ቤት ቀርቦ የነበረው የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሶስትዮሽ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ህብረት እንዲመለስ መወሰኑ ይታወቃል።
በሁሉም የምክር ቤት አባላት ዘንድ የተገኘ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው።ቋሚ አባላቱም ሁሉም በሚባልበት ደረጃ በአፍሪካ ህብረት የተጀመረው ድርድር እንዲቀጥል ሀሳብ ሰጥተዋል።
ከዚህ በኋላ የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካ እንዲታይ የሚደረግ ሆኗሎ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ።
በኒዮርክ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት ሰላማዊ ሰልፍም ትልቅ ጫና የነበረውና የሚያስመሰግን ተግባር ነው ብለዋል አምባሳደር ዲና።
በናይል ተፋሰስ አገሮች አምባሳደሮች ውይይት መደረጉን ገልፀው፤ የሱዳንና ግብፅ ግድቡን የፀጥታ ጉዳይ ለማድረግ የተሞከረበት አግባብ ትክክል እንዳልሆነና ግድቡ የልማት አጀንዳ እንደሆነ አምባሳደሮቹ ተነጋግረው ተግባብተዋል ብለዋል።
የፀጥታ ምክር ቤት ጉዳዩን አይመለከተውም፤ አረብ ሊግ የአፍሪካ ህብረትን የመናቅ እና አሳንሶ የማየት ጉዳይ እንደሆ አምባሳደሮቹ መግለጻቸውን አስታውቀዋል።
በትግራይ የተኩስ አቁም ውሳኔ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለውጭ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፃ ተደርጓል።
የዘር ወቅት መሆኑ ከተያዩ አካላት ጋር ለመነጋገር ያለ ፍላጎትና የህወሓት ኃይል የስጋት ምንጭ እንዳልሆነ በመንግሥት በመታመኑ የተኩስ አቁም ውሳኔ እንዲወሰን ምክንያት እንደሆነ ተገልፆላቸዋል ነው ያሉት።
የበረራ ፈቃድ በአዲስ አበባ በኩል እንዲገቡና እንዲወጡ በረራዎች ተፈቅደዋል ነው ያሉት። የተከዜ ድልድይን ለመጠገን እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።