የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30/2013 (ኢዜአ) የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዷል።
በዚህም የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባርን ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዓለም አቀፉ የልማት ማህበርና በኢትዮጵያ መካከል ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲውል የተፈረሙ አራት የብድር ስምምነቶችን አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቻርተርና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር የተስማማችባቸውን ሁለት የመንገድ ደህንነት ቻርተሮችንም አፅድቋል።