ቀጥታ፡

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳውቅ ገለጸ

ሰኔ 28 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳውቅ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ሶሊያና ሽመልስ በሰጡት መግለጫ ድምጽ በተሰጠባቸው ሁሉም የምርጫ ክልሎች ውጤት ተጠቃሎ ገብቷል።

"ባለፈው ሳምንት ለቦርዱ ያልደረሱ 30 የምርጫ ውጤት አሁን ተጠቃለው ገብተዋል" ብለዋል።

በመሆኑም በዚህ ሳምንት የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት ቦርዱ የሚያስታውቅ መሆኑን አመልክተዋል።

ሃላፊዋ በመግለጫቸው ተቋርጦ የነበረው የቁጫ ምርጫ ክልል የድምጽ ቆጠራ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በክልሉ የተወዳደሩት ሰባቱም የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት ቆጠራ መጀመሩን ገልጸዋል። በነገሌ የምርጫ ክልል ድምፅ ያልተሰጠባቸው 30 የምርጫ ጣቢያዎች በቀጣይ ሀሙስ ሀምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ድምጽ ይሰጣል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም