ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትየሰጡት ማብራሪያ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትየሰጡት ማብራሪያ

አዲስ አበባ ሰኔ 28/2013(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት የሰጡት ማብራሪያ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ፤
የህወሃት ጁንታው ወታደር በማዘጋጀት አገር ለማፍረስ ብዙ ዝግጀት አድርጓል።
በገንዘብና ትጥቅ በማገዝ ቅጥረኞችን በማስፋፋት ግጭት በመፍጠር አገር ለማተራመስ ጥረት አድርጓል፤
የትግራይ ህዝብ በብዙ ችግር ውስጥም ሆኖ ለጦርነት ሲንቀሳቅስ ኖሯል፤ በመቀጠልም ጁንታው የሰሜን እዝን ወጋ፡ ሰራዊቱን ለማዋረድ የሄደበት ርቀትም የከፋ ነበር።
ጁንታው ሰሜን እዝን ካጠቃ በኋላም የግዛት ማስፋፋት አላማም ነበረው። ይህንን ለመከላከል ነበር መንግስት ወደ ህግ ማስከበር የገባው።
መንግስት ህግ ካስከበረ በኋላ በክልሉ መልሶ ግንባታና ሰብአዊ ድጋፍ እያደረገ ህዝቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ብዙ ጥረት አድርጓል።
በብዙ ድካምና መስዋእትነት ጭምር በኢትዮጵያ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር የነበረው የጁንታው ጥረትና እቅድ ከሽፏል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ይህንን ሁሉ ጥረት አድርጎ በክልሉ ሰላም ለማስፈን የነበረው ጥረት ግን ምላሹ "ባጎረስኩ እጀን ተነከስኩ" ሆኗል።
የትግራይ ሁኔታ በተለያዩ አካላት ግጭቱ እንዲቆም አይፈለግም፤ "ለቅሶ ከፍየሏ በላይ ነው" እንደሚባለው ለኢትዮጵያ አስበው ነው እንዳንል ሌሎች አካባቢዎች ያሉትን ችግሮች የሚያነሳ አካል የለም።
"ለዶሮ በሽታ በሬ ማረድ አያስፈልግም፤ ከበሽታው ልክ በላይ ጊዜ ማባከን አያስፈልግም" ብለን የጥሞና ጊዜ መኖር አለበት የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰን ነው ሰራዊት ያስወጣነው።
ከትግራይ ቀደም ብለን ነው ከአንድ ወር በፊት ትጥቅና ወታደር ማስወጣት የጀመርነው።
"ለዶሮዋ ህመም በሬ አናርድም" በማለት ቀደም ብለን ውይይት በማድረግ ነው የጥሞና ጊዜ እንስጥ በማለት ነው ከትግራይ ሰራዊት ያስወጣነው።
የመንግስት ሃይሎች ከአካባቢው ከወጡ በኋላ በትግራይ ብዙ ጥፋቶች እየተፈፀሙ ነው፤ ንፁሃን በሃይማኖትና ማንነታቸው እየተገደሉ ነው።