ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአበበች ጎበና ህልፈተ ህይወት የተሰማቸው ሃዘን ገለፁ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአበበች ጎበና ህልፈተ ህይወት የተሰማቸው ሃዘን ገለፁ
ሰኔ 27/2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ህልፈተ ህይወት የተሰማቸው ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኢትዮጵያ "የርህራሄ ተምሳሌት የነበሩት አበበች ጎበናን እልፈተ ህይወት ስሰማ እጅግ አዝኛለሁ" ብለዋል።
ለቤተሰቦቻቸው: ለወዳጆቻቸው እና በሕይወታቸው ላይ ተጽዕኖ ለነበራቸው ሁሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ ሲሉ ገልጸዋል።
የበርካታ አሳዳጊ ያጡ ህፃናት እናት የሆኑትና በበጎ አድራጎታቸው የሚታወቁት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ዛሬ ጠዋት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።