የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ
ሀዋሳ፤ ሰኔ 26/3013 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት አምስተኛው ዙር ስድስተኛ ዓመት የስራ ዘመን 12ኛው መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ።
ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው አንድ መደበኛና አንድ አስቸኳይ ረቂቅ ቃለ ጉባኤን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
እንዲሁም በሚቀርበው የክልሉ የ2013 በጀት ዓመት የእስካሁን የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ እንደሚወያይ ተመልክቷል።
በጉባኤው የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት እየተሳተፉ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከሥፍራው ዘግቧል።