በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና በፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የሚመራ የልኡካን ቡድን ወደ አስመራ አቅንቷል

63
አዲስ አበባ ሐምሌ 30/2010 በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የሚመራ የልኡካን ቡድን በኤርትራ በዳውድ ኢብሳ የሚመራውን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ ጋር ለመወያየት ዛሬ ወደ አስመራ አቅንቷል። የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ኃላፊው እንዳሉት፤ መንግስት ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ አገር ገብተው በሰላም እንዲታገሉ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ፍጻሜ ለማድረስ እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል። እስካሁን የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ወደ አገር ካልገባው የኦነግ ክንፍ ጋር ውይይት ለማድረግ ነው ልኡኩ ዛሬ ማለዳ ወደ አስመራ ያቀናው። ዶክተር ነገሪ ወይይቱም ከሰዓት እንደሚጀምር ነው የገለጹት። እስካሁን በተደረገው የሰላም ጥሪ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰ ሲሆን፤ ግንቦት 7 ለመምጣት በዝግት ላይ እንደሆነ ገለጸዋል። በተመሳሳይ ቢሮ ኃላፊ በሱማሌ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች ሰላማቸውን እንዲያስጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል። የአዋሳኝ አካባቢ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም