ቀጥታ፡

ቦርዱ ከምርጫ ክልሎች የመጡ ድምጾችን በምን መልኩ እንደሚረከብ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አስጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከየምርጫ ክልሎች ወደ ማዕከል የሚመጡ የዜጎችን ድምፅ በምን መልኩ አረጋግጦ እንደሚረከብ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አስጎበኘ።

ቦርዱ ከ378 ምርጫ ክልሎች የተረከበውን የዜጎች ድምጽ በምን መልኩ እንደሚያጣራ ለመገናኛ ብዘሃን ባለሙያዎች አስጎብኝቷል።

ቦርዱ መረጃ መዝጋቢ፣ አጣሪ፣ ኦዲተር፣ መረጃውን ወደ መረጃ ቋት የሚልክና ተረካቢ ቡድን አማካኝነት ከየምርጫ ክልል የመጡ ድምጾችን አጣርቶ እየተረከበ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም