አምቦ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 524 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል እየተዘጋጀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 524 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል እየተዘጋጀ ነው
አምቦ፣ ሰኔ 18 ቀን 2013 (ኢዜአ) አምቦ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 524 አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራር ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ማንደፍሮ ለገሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት 3ሺህ 524 አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ትምህርት ለመጀመር ተጨማሪ የመምህራን ቅጥር ማካሄዱን ተናግረዋል።
ያልተጠናቀቁ ህንጻዎችን የማጠናቀቅና የሚታደሱትን የማደስ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነም አመልክተዋል።
በትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ስራው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ራሱን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንዲጠብቅ ለማድረግ ከከተማ አስተዳደርና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ በሚቀበላቸው ተማሪዎች አጠቃላይ የቅበላ አቅሙ ከ27 ሺህ በላይ እንደሚደርስ አመላክተዋል።
ወደ ዩኒቨርሲቲው ለሚመጡ ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ጀምሮ በትራንስፖርት አቅርቦት የተደገፈ አቀባበል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 24 እና 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎችን የሚቀበል ይሆናል።