ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና ሌሎች የዘርፍ ኮሚሽኖች የቀረበለትን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18 ቀን 2013 (ኢዜአ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና ሌሎች የዘርፍ ኮሚሽኖች የቀረቡለትን ሹመት አጸደቀ።


ምክር ቤቱ ወይዘሮ ራኬብ መሰለን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል።

ወይዘሮ መስከረም ገስጥን የሴቶችና ህጻናት መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር፣ ወይዘሪት እርግበ ገብረሃዋሪያን የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል።


ዶክተር አብዲ ጅብሪል ደግሞ የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም