የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ በማከናወን በእለቱ ደም ለማፋሰስ ያቀዱ ኃይሎችን ሴራ አክሽፏል--አምባሳደር ዲና ሙፍቲ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ በማከናወን በእለቱ ደም ለማፋሰስ ያቀዱ ኃይሎችን ሴራ አክሽፏል--አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ሰኔ 17 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫውን በሰላማዊ መንገድ በማከናወን በእለቱ ደም ለማፋሰስ ያቀዱ ኃይሎችን ሴራ አክሽፏል ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
ቃል አቀባዩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በምርጫው ወቅትና ከምርጫ በኋላ በአገሪቱ ደም እንዲፋሰስ የሚፈልጉ ኃይሎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።በምርጫው እለት የነበረውን ሂደት በርካታ አገር አቀፍና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ሽፋን የሰጡት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ምርጫው ታማኝና ሰላማዊ እንደነበር ማረጋገጡንም አክለዋል።ሌሎች አገራት ከኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት በርካታ ትምህርት እንሚቀስሙ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡