ቀጥታ፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምርጫ ጣቢያ 01 በመገኘት ድምጽ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14 ቀን 2013 (ኢዜአ) የእስልምና ሃይማኖት መምህሩ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምርጫ ጣቢያ 01 በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

የአረንጓደ አሻራ (የግሪን ሌጋሲ) አምባሳደሩ ኡስታዝ አቡበከር ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ችግኝ ተክለዋል።

የዚህ ታሪካዊ ወቅት አካል በመሆናቸው እና ድምጻቸውን በመስጠታቸው እንዲሁም ችግኝ በመትከላቸው መደስታቸውን ገልጸዋል።

"የተሻለ አገር ይዘን ለመሻገር ድምጻችንን መስጠት ስለሚገባን ካርድ የወሰድን ሁሉ ድምፅ በመስጠት ዋጋ እንስጠው" ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሁሉም በሀሳብ የበላይነት አምኖ የተስማማበትን ፓርቲ በመምረጥ የራሱን መብት በመጠቀም የአገሩንም የወደፊት እጣ ፈንታ መወሰን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

"ትውልዱን ለማሻገር የጀመርነውን ጉዞ ለማሳለጥ ዛሬ ላይ ድምጻችንን በመስጠት ማስቀጠል አለብን" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም