የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱን እየታዘበ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱን እየታዘበ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14 ቀን 2013 (ኢዜአ) በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ የተመራው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱን እየታዘበ ነው።
የህብረቱ ታዛቢዎች በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የምርጫ ክልል 21/22 ምርጫ ጣቢያ 4 እና 5 የምርጫ ሂደቱን በመታዘብ ላይ ናቸው።
በዘንድሮው ምርጫ 45 ሺህ የአገር ውስጥ ታዛቢዎች በታዛቢነት የሚገኙ ሲሆን 45 አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችም ይገኛሉ።
ከ120 ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች፣ የአፍሪካ ህብረትና የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ምርጫውን በመታዘብ ላይ ናቸው።
በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ 46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ፉክክሩ ላይ ተሳትፈዋል።
37 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሕዝብ ለመራጭነት ተመዝግቧል፤ 9 ሺህ 327 ዕጩዎች ደግሞ ለህዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች መቅረባቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።