በአፋር ፈንቲ ረሱ ዞን ምርጫው እየተካሄደ ይገኛል

56

ሰመራ፤ ሰኔ 14/2013(ኢዜአ) ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን እየተካሄደ ነው።

ሪፖርተራችን  በዞኑ ጉሊና ወረዳ ከለዋን ከተማ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ እንደተመለከተው ታዛቢዎች ባሉበት  ኮሮጆችች ባዶ መሆናቸው ተረጋግጦ ህዝቡ በሰልፍ ተራውን እየተጠባበቀ ጽምጽ እየሰጠ ይገኛል።

የምርጫው ሂደትም ሰላማዊና የተረጋጋ መሆኑን ተመልክቷል።

የዞኑ ምርጫ አስተባባሪ አቶ ሙጀሂድ አላ እንደገለጹት፤ በዞኑ በተቋቋሙ 184 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ተጀምሯል።

በዞኑ ለመራጭነት የተመዘገበ ከ276ሺህ በላይ ህዝብ ድምጹን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም